በአማራ እና ትግራይ ክልል ለሚገኙ አርሶ አደሮች የአትክልት እና ፍራፍሬ ዘር ድጋፍ ተደረገ።

17

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኔዜርላንድ የልማት ደርጅት በግጭት እና ድርቅ ለተጎዱ በአማራ እና ትግራይ ክልል ለሚገኙ አራት ሺህ አርሶ አደሮች የሚከፋፈል የአትክልት እና ፍራፍሬ ዘር ድጋፍ አደረገ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን በወቅቱ እደገለጹት ድጋፉ በግጭት እና ድርቅ የተጎዱ አከባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም እና የአርሶ አደሩን ሕይወት ለመደገፍ ያለመ ነው።

ድጋፉ የቀይ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ቃሪያ እና ሀባብ ዘር መሆኑን ገልጸዋል። በተደረገው ድጋፍም 371 ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚቻል ዶክተር መለስ ተናግረዋል።

የኔዜርላንድ የልማት ደርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም በበኩላቸው ድርጅቱ የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ፕሬስ ድረጅት እንደዘገበው ድርጅቱ ከዘር ድጋፍ ባለፈም አጠቃላይ የአትክልት እና ፍራፍሬ አመራረት ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት አባቶች ስለሰላም መስበክ እንደሚገባቸው የኮረም ከተማ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ።
Next articleየገቢዎች ሚኒስቴር፣ አማራ ባንክ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር በጋራ አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት አደረጉ።