የመማር ማስተማሩ ሥራ በአግባቡ እየተከናወነ መኾኑን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

17

ወልድያ: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት በክልሉ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ዘግይተውም ቢሆን መቀበላቸው ይታወሳል። ወልድያ ዩኒቨርሲቲም ተማሪዎቹን ጥር ወር መጀመሪያ ላይ የተቀበለ ሲኾን አሚኮ የግቢውን የመማር ማስተማር ሁኔታ ቃኝቷል።

አሚኮ ያነጋገራቸው ተማሪዎች ወደ ግቢ ሲመጡ ስጋት አድሮባቸው እንደነበር ነው የገለጹት። ይሁን እንጂ አሁን ላይ ፍፁም ሰላማዊ የኾነ መማር ማስተማር እንዳለ ነው የነገሩን።
ዘግይተው በመግባታቸው የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥድፊያ እንደሚታይበት ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ቤተመፃሕፍትና የሚሰጣቸውን የንባብ መፃሕፍት በመጠቀም ተገቢውን እውቀት ይዘው ለመውጣት ጥረት እያደረጉ እንደኾነም አስረድተዋል።

የዩኒቨርሲቲው የትምህርት እና ምርምር ምክትል ኘሬዚዳንት ሱልጣን መሐመድ (ዶ•ር) የመማር ማስተማሩ ሥራ በመጀመሩ የግቢው ድባብ ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ተቀይሯል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ከግቢው ፖሊሶች እና ከፌዴራል ፖሊሶች ጋር በማቀናጀት የራሳቸውን አካባቢ እንዲጠብቁ እና የግቢው ሰላም እንዳይናጋ የድርሻቸውን እንዲወጡ መደረጉ አሁን ላለው ሰላማዊ መማር ማስተማር ስኬት አበርክቶ አለው ብለዋል።
ወላጆች የልጆቻቸው ደኅንነት ሊያሰጋቸው እንደማይገባም ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ እና ከኩዌት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ።
Next articleየሃይማኖት አባቶች ስለሰላም መስበክ እንደሚገባቸው የኮረም ከተማ የሃይማኖት አባቶች አሳሰቡ።