
ባሕር ዳር: የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ እና ከኩዌት አምባሳደሮች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በወቅቱም ኢትዮጵያ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ እና ዮርዳኖስ መካከል የተፈረመው የሠራተኛ ስምሪት ስምምነት በሚኒስትሮች ምክር ቤት መጽደቁን አንስተዋል። መሰል ስምምነቶች ኢትዮጵያ ከዮርዳኖስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደ ድልድይ ሊያገለግሉ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
የኩዌት አምባሳደር በበኩላቸው በቅርቡ የሠራተኛ ስምሪት ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ይፈረማል ሲሉ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!