
ባሕር ዳር፡ የካቲት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ የክልሉ የሰላም ጉዳይ ላይ መልእክት አስተላልፏል።
ሙሉ መልእክቱ ቀጥሎ ቀርቧል፦
ሕግ ማስከበር ዋነኛ ግቡ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ ነው! የሕግ የበላይነት መረጋገጥ የአንድን ማኅበረሰብ የተረጋጋ ዘላቂ ሕይወት ለመመስረትና ለመጭዉም ትዉልድ የሚተርፍ አሻራ ለማኖር ወሳኝ ነዉ።
በግጭት ውስጥ የቆየ ማኅበረሰብ ለሕይወቱ፣ ለንብረቱና አጠቃላይ የኑሮዉ ዋስትና ስለማይኖረዉ የእለት ልብሱንና ጉርሱን ከመሻት አልፎ የዘላቂ ልማት አላማን ታሳቢ ያደረገ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ዉስጥ ሊሰማራ አይችልም።
ሕገ-ወጥነትንና ስርዓት አልበኝነት እንደሕዝብ አለመረጋጋትን የሚያስከትል በመሆኑ መቆጣጠር ካልተቻለ ሁሉንም ነገር ደረጃ በደረጃ ከመንግሥትና ከሕዝብ እጅ እንዲወጣ ያደርጋል።
ይህ ሁኔታ እንዳይፈጠር እና ሲፈጠር ለመቆጣጠር መንግስት የሚጠበቅበትን ሕግ የማስከበር ሥራ ይሠራል።
እዉነታዉ ይህ ሁኖ እያለ አንዳንድ አጥፊ ቡድኖችና ግለሰቦች የመንግስትን ሆደ ሰፊነት ቦታ ባለመስጠት በሕዝብ ላይ ያልተገባ ሕገወጥ ተግባር ሲፈጽሙ ይታያሉ። እነዚህ ቡድኖች እና ግለሰቦች ራሳቸዉን ከሕግ በላይ በማድረግ በተለያዩ ቦታዎች ያልተገባ ተግባር ከመፈጸም ባለፈ መንግስት የእለት ተእለት ተግባሩን ለሕዝብ እንዳያደርስ እንቅፋት እየፈጠሩ ቆይተዋል።
በጽንፈኞች መሪ ተዋናኝነት በክልላችን በቅርብ ያጋጠመዉ የሰላም መደፍረስ ምክንያት የዜጎች እንቅስቃሴ የተገታበት፣ የመንግሥት ተቋማት ሥራ የተስተጓጎለበትና የተዘረፉበት፣ ከሁሉ በላይ አዉቀዉም ይሁን ሳያዉቁ የክልላችን ወጣቶች የጽንፈኞች ሀሳብ ተሸካሚ ሁነዉ የሕይወት ዋጋ የከፈሉበትን ሁኔታ አስተናግደናል።
ይህ እኩይ ተግባራቸዉም በጀግናዉ መከላከያ ሠራዊታችን እና በክልላችን የጸጥታ ኀይል በጋራ በሠሩት ታሪካዊ ተግባር ፍላጎታቸዉ ሳይሳካ መክኗል። ይሁን እንጅ ይህ አጥፊ ቡድን የራሱን ግፍ እንደቅዱስ ተግባር በመቁጠር የመከላከያ ሰራዊታችን ምት መቋቋም ሲያቅተዉ የንጹሀንን ካባ ለብሶ ሙሾ ማዉረድ ዛሬም የዘለቀዉ የእለት ከእለት ተግባሩ አድርጎታል።
የዚህ እኩይ ተግባሩ ዋነኛ ማሳለጫዉም ከዉጭና ከዉስጥ በተዘረጋ የጥፋት ኔትወርክ ተጠቅሞ እየተወሰደበት ያለዉን ሕግ የማስከበር ዘመቻ ሕዝብ ውስጥ በመወሸቅና ራሱን የሕዝብ ብቸኛ ጠበቃ በማስመሰል ማስተጓጎል ነዉ። የቡድኑ ባሕሪም ሲመታ የንጹሀን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ አረመኒያዊ ተግባሩን ሲፈጽም ደግሞ እንደጀብዱ የሚቆጥሩ አጥፊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ማራገብ ነዉ።
በአሁኑ ወቅት ጽንፈኛ ቡድኑ ሴራዉ በአደባባይ ተገልጦበት፤ ጉልበቱ ከድቶት አለኝ የሚለዉን ገዥ ቦታ ሳይቀር ለመከላከያ ሠራዊታችን እና ለክልላችን የጸጥታ ኀይል በማስረከብ በየጉሬዉ ተደብቆ ይገኛል። ቡድኑም አንዳንዴ ከተደበቀበት ጉሬ በመዉጣት የዉጭና የዉስጥ ደጋፊዎችን አለሁ ለማለት ብቻ እኩይ ተግባሩን እየፈጸመ ይገኛል።
በክልላችን የተጀመረው ሕግ ማስከበር ስሥራም ዋና ዓላማዉም የሕዝብን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ ታልሞ የሚተገበር በመሆኑ በቀጣይም ህግ የማስከበር ሥራዉ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ለዚህም ኅብረተሰቡ ከመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ጎን ሆኖ ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠሉ አመርቂ ዉጤቶች ተመዝገባዋል። በዉጤቱም በአብዛኛዉ የክልላችን አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል።
በተገኘዉ አንጻራዊ ሰላምም በጸጥታ መደፍረስ