ግዙፉ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ ተመርቆ ምርት ማምረት እንደሚጀምር የክልሉ መንግሥት ገለጸ።

160

ባሕር ዳር፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ የተገነባ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ነው።

ፋብሪካው በአፍሪካ ግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን በቀን ከ10ሺ ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም አለው።

ለሚ ሲሚንቶ በግንባታ ሒደት ላይ ሆኖ ለበርካታ ወገኖች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን ግንባታው ተጠናቆ ምርት ማምረት ሲጀምር ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ይችላል።

በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን ከ130 ሺህ እስከ 150 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአጠቃላይ ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ምርት ማምረት ሲጀመር የኢትዮጵያን የሲሚንቶ ፍላጎት 50 በመቶ መሸፈን የሚችል ነው።

ተጠባቂው ግዙፉ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቅርቡ ተመርቆ ምርት ማምረት ይጀምራል ሲል የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ዝግጁ ነን” የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት
Next article“ሕግ ማስከበር ዋነኛ ግቡ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ ነው!” የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ