“ሥልጠና አጠናቃችሁ የአድማ ብተና አባላትን ስትቀላቀሉ የሕዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ አደራ ተጥሎባችኋል” የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን

44

ወልድያ፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሥልጠና አጠናቀው የአድማ ብተና አባላትን የተቀላቀሉ የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ሰሜን ወሎ ዞን እና ወልድያ ከተማ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር “በሴራ በተጠለፈ ኃይል የክልሉ ሕዝብ እንዲታመስ እድል ልትሰጡት አይገባም ብለዋል። የዞናችንን እና የወልድያ ከተማን ሕዝብ ሰላሙ ተጠብቆ እንዲቆይ ለመሥራት በመምጣታችሁ ደስ ብሎናል” ብለዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ክልላችን የልማት ሥራው ተስተጓጉሏል። አርሶ አደሮችም ያመረቱትን ምርት በተገቢ ዋጋ ለመሸጥ አልቻሉም። ሕዝቡ እንደልቡ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ፣ መሥራት፣ መነገድ አልቻለም። ስለዚህ ይህን የክልሉን ሕዝብ መከራ ለማቅለል ፀጥታውን የማረጋጋት ሥራ የእናንተ ኀላፊነት ነው እና የሕዝባችሁን አደራ ልትውጡ ይገባል ነው ያሉት።

ከሌሎች አካላት ጋር በመቀናጀት የሚሰጣችሁን ግዳጅ እና ኀላፊነት በብቃት ልትወጡ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል፡፡ የእናንተ መቀላቀል ለመከላከያ ትልቅ አቅም ነው ያሉት የሰሜን ወሎ ዞን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ እና የሰሜን ምስራቅ እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሻምበል ፈረደ የክልሉን ሕዝብ ሰላም ለማረጋገጥ መከላከያ ከእናንተ ጋረ በጥምረት ይሠራል ነው ያሉት

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየበለስ-መካነ ብርሃን የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚኮን ተገለጸ።
Next articleየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቀቀ።