
ባሕር ዳር፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሃ-ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ከርዕሰ ጉዳይ መረጣና አሳታፊነት አንጻር የመድረኩን የአምስት ዓመት ጉዞ ቃኝተዋል፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) በበኩላቸው አዲስ ወግ ለፖሊሲ ግብዓት ሆኖ ማገልገሉን ጠቁመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አዲስ ወግ ቀጣይነት ያለው የውይይት ባሕልን ያዳበረ ነው በማለት የገለፁ ሲሆን የታሪክ ምሁሩ ታምራት ሀይሌ (ዶ.ር) በበኩላቸው የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውይይት ታሪክ ዳሰዋል፡፡
ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን አዲስ ወግ በመገናኛ ብዙኃን የተሰጠውን ሽፋን የተመለከተ ጥናታዊ ዳሰሳ ሲያቀርብ፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ከሚዲያዎች ተመድበው የሚሠሩ ቋሚ ዘጋቢዎችም መድረኩን በመዘገብ የነበራቸውን ልምድ ማካፈላቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!