ደቡብ ወሎ ዞን 23ሽ 859 ሄክታር መሬት በአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ መሸፈኑ ተገለጸ።

15

ደሴ: የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን 23ሽ 859 ሄክታር መሬት በአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ መሸፈኑ ተገልጿል።የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምርያ የተፈጥሮ ሃብት ልማት፣ ጥበቃ እና አጠቃቀም ቡድን መሪ መገርሳ ተሾመ በ15 ወረዳዎች፣ በ285 ቀበሌዎች እና በ778 ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ሥራው መከናወኑን ተናግረዋል።

የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራው ለ23 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተሠራ መኾኑንም ቡድን መሪው ተናግረዋል። ሥራው ተጠናክሮም እንደሚቀጥል መጠቀሱንም የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከላሊበላ – ሙጃ – ቆቦ አስፓልት መንገድ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።
Next article“ድርቁን እያሸነፍን ነው” የአበርገሌ ወረዳ አርሶ አደሮች።