ከላሊበላ – ሙጃ – ቆቦ አስፓልት መንገድ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

29

ባሕር ዳር፡ የካቲት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለበርካታ ዓመታት የማኅበረሰቡ ጥያቄ የነበረው ከላሊበላ – ሙጃ – ቆቦ አስፓልት መንገድ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።

የመንገድ ፕሮጀክቱን የቡግና ምርጫ ጣቢያ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወካይ ወ/ሮ ቅድስት አርዓያ በተገኙበት የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል ፡፡ በጉብኝቱም የላስታ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ጌታቸው መልሴ እንደገለፁት የመንገዱ ሥራው ለብዙ ዓመታት የኅብረሰቡ ጥያቄ የነበረ እና ምላሽ ያገኘ ፕሮጀክት በመሆኑ ያለምንም እንቅፋት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ማኅበረሰቡ ምንም የካሳ ግምት ሳይከፈለው እያደረገ ላለው ትብብር እና ፕሮጀክቱ በዚህ ሰዓት እያደረገ ላለው ሥራ ትልቅ መስጋና አቅርበዋል ፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጅነር ሞላ አድማሱ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለመጨረስ እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል። የካሳ ግምት መዘግየት እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገልፀዋል ፡፡

ወ/ሮ ቅድስት ዓርዓያ በጉብኝቱ እንደገለፁት በዚህ ወቅት ፕሮጀክቱ ያለምንም ችግር እየተሠራ በመሆኑ ለማኅረሰቡና ለፕሮጀክት አስተባባሪወች ምስጋና አቅርበዋል። ትልልቅ ፕሮጀክቶች ከገጠር ወደ ከተማ ሲደርሱ የሚዘገይበትና ከካሳ ግምት ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ችግሮች እየተፈጠሩ በመሆኑ ለዚህ ፕሮጀክት ይህ አይነት ችግር እንዳይገጥመው ከወዲሁ የካሳ ግምቶች እንዲሠሩ እና ካሳ ለተሠራላቸው አርሶ አደሮች ክፈያዎች በፍጥነት እንደዲፈፀሙ ግፊት እንደሚያደረጉ ተናግረዋል ፡፡ መረጃው የላስታ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባለፉት ስድስት ወራት 176 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ከ1 ሺህ 280 በላይ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደዋል” አቶ እንድሪስ አብዱ
Next articleደቡብ ወሎ ዞን 23ሽ 859 ሄክታር መሬት በአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ መሸፈኑ ተገለጸ።