
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ በሐይቅ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
ሀብት የመፍጠር ጉዞ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
በመድረኩ የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ባንቺአምላክ ገብረ ማሪያም፣ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ መሀመድ አሊ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሀና አለባቸው እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል። መረጃው የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!