በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነዉ።

95

ደብረ ብርሃን: የካቲት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘዉ በዞኑ ያጋጠመዉን የሰላም እጦት ዘለቂ በኾነ መንገድ መፍትሔ ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ነው ተብሏል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ ዞኑ ያጋጠመውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግር ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ የሚያነሳቸዉን መሠረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መንግሥት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ሰላማዊ ውይይት በማድረግ መፍታት እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።

በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ በመከላከያ ሠራዊት የ105ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ እና የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና የአረርቲ ከተማ የኮማንድ ፖስት አሥተባባሪ ብርጋዴር ጀኔራል ሞሲሳ ቶሎሳን ጨምሮ የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ ከተማ አሥተዳደር ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
Next articleበሐይቅ ከተማ አሥተዳደር ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።