
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህታማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ በኮረም ከተማ አስተዳደር ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ፈንታው ፈጠነ፣ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ሕዝባዊ ውይይቱ የተጀመሩ ሁለንተናዊ ሀገራዊ የድል ጉዞዎችን ለማጠናከር እና ተግዳሮቶችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለመ ነው ተብሏል። በውይይቱ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚነሱ ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!