በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የተገኙበት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

44

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ የውይይት መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚስተዋሉ የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት እየተደረገባቸው መኾኑን የዘገበው ፋብኮ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሳምንቱ በታሪክ! የማስታወቂያ ሥራ ፈር ቀዳጁ ውብሸት ወርቃለማሁ
Next article160 ሜትር የሚረዝመው የበለገዝ ወንዝ ድልድይ ግንባታ መጠናቀቁን የመከላከያ ኮንስትራክሽን አስታወቀ።