
ባሕር ዳር፡ የካቲት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዱባይ እና በሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር የተዘጋጀው ይህ መርሃ-ግብር “ኮሚኒቲያችን ለጋራ እንድነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ ለ10ኛ ግዜ ነው እየተከበረ ያለው፡፡
መርሃ-ግብሩ ዜጎች ከሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር እንዲያጠናክሩ፤ መብትና ጥቅማቸው እንዲከበር እንዲሁም ዳያስፖራው በሀገሩ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወትም ተገልጿል፡፡
ኢቢሲ እንደዘገበው በተባበሩት ዐረብ ኢምሬቶች 150 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!