የተሟላ ከወለድ ነፃ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ለደንበኞቹ እየሰጠ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገለጸ።

22

አዲስ አበባ፡ የካቲት 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር 10ኛ ዓመት የመዝጊያ መርሐ ግብር ዛሬ አካሂዷል።

ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት “ውጤታማ ምዕራፍ ብሩህ ተስፋ” በሚል መሪ መልእክት ላለፉት ሦስት ወራት የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በመቅረጽ ከደንበኞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሲያከብር መቆየቱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ገልጸዋል።

ባንኩ በመላ ሀገሪቱ የተሟላ ከወለድ ነፃ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ለደንበኞቹ እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ላለፉት 10 ዓመታት የሸሪዓ ሕግጋትን ተከትሎ ሲሰጥ መቆየቱን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት ኑሪ ሁሴን ተናግረዋል።

አሁን ባንኩ የሲቢኢ ኑር ተቀማጭ ገንዘቡን ከ107 ቢልዮን ብር በላይ ማድረሱን አቶ ኑሪ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ እዮብ ርስቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article27ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በ9 ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አጸደቀ።
Next article“የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የሰላም አማራጮችን በስፋት ያመላከተ ነበር” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ