ኢትዮጵያ ሁለት ቀጠናዊ ውድድሮች የማዘጋጀት ኃላፊነት ተሰጣት።

84

ባሕር ዳር: የካቲት 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሴካፋ በኬንያ ሞምባሳ እያካሄደው ባለው ጠቅላላ ጉባኤ በዚህ ዓመት የተለያዩ ውድድሮች እንዲያዘጋጁ የመረጣቸው ሀገራት ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ የካፍ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ፣ የሴካፋ የማጣሪያ ውድድር እና ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።

ዩጋንዳ የአፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ፣ ታንዛኒያ ደግሞ የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎችን የምታስተናግድ ሲሆን ዛንዚባር የ2024 የሴካፋ ዋንጫን የማስተናገድ መብት ተሰጧታል ሲል ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለፉት ተከታታይ ዓመታት ባከናወኗቸው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ተጠቃሚ መኾናቸውን አርሶ አደሮች ገለጹ።
Next articleየልማት ድርጅቶች እያደገ በመጣው የኢንቨስትመንት አማራጭ ተወዳዳሪ እንዲኾኑ እየተሠራ መኾኑን ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን ገለጹ።