የአማራ ክልል ምክር ቤት የተጓደሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትን የሚያሟሉ አዳዲስ አባላትን ሰየመ።

82

ባሕር ዳር: የካቲት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአሠራር ሕጉ መሠረት ከየአካባቢው በተውጣጡ የሕዝብ ተወካዮች የሚሟላ ሲኾን በተለያየ ምክንያት ከአማራ ክልል የተጓደሉ አባላትን ለመተካት የክልሉ ምክር ቤት ተተኪዎችን መርጦ አጽድቋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአማራ ክልል የተጓደሉ አባላትን ለክልሉ ምክር ቤት በደብዳቤ እንዳሳወቀ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲኾኑ ተሰይመዋል።

በአዲስ የተሰየሙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አስፈላጊውን የሥራ ጥንካሬ እና የአካባቢ ስብጥር መሠረት ተደርጎ የተመረጡ ስለመኾኑም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም መርሐ ግብር መካከለኛውን እና አሠባሣቢውን ትርክት በመፍጠር ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው” የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ
Next articleከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ስንዴ መሸፈኑን የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ገለጸ።