በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ኮንፍረንስ በሰመራ መካሄድ ጀመረ።

39

ባሕር ዳር: የካቲት 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልሎች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ኮንፍረንስ በሰመራ እየተካሄደ ነው።

በኮንፍረንሱ ከሶስቱም ክልሎች የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ ከነጋዴዎች ማኅበራትና ከግል ዘርፍ የተውጣጡ አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኮንፍረንሱ ዓላማ ባለፉት ጊዜያት በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት የተቀዛቀዘውን የንግድ እንቅሰቃሴ መልሶ ለማነቃቃት ሲሆን የግል የንግድ ሴክተሩም መንቀሳቀስ እንዲችል ያለመ ነው።

መርኃ ግብሩን የሰላም ሚኒስቴር፣ የአፋር ንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በዘርፉ የሚንቀሳቀስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትብብር ያዘጋጁት መሆኑም ተመላክቷል።

በኮንፍረንሱ የሰላም ሚኒስቴርና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የአፋር ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊዎች ታድመዋል። መረጃው የኢዜአ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድ የባሕር በር ስምምነት በሦስተኛ አካላት አይቀየርም” ዒሳ ካይድ መሐሙድ(ዶ.ር)
Next articleየኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች የሚያስከብሩ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ተከናውነዋል።