
ባሕር ዳር፡ የካቲት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሶማሊላንድ መንግሥት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈራረመውን የመግባቢያ ሥምምነት ዳር ለማድረስ ቁርጠኛ መኾኑን አስታውቋል።
የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ በሂ ሀገራቸው ከወር በፊት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈራረመችውን የመግባቢያ ሥምምነት ዳር ለማድረስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናዎኗን አስታውቀዋል፡፡
እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ሥምምነቱን ዳር የሚያደርስ ቴክኒካል ኮሚቴ ማዋቀር፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች ቡድን ማደራጀት እና ከፍተኛ የሕገ መንግሥት አማካሪ ግብረ ኀይል የማደራጀት ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቁመዋል ሲል ኢንሳይድ አፍሪካ አስነብቧል፡፡
በታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!