መልካም አሥተዳደርን በማስፈን የአካባቢያቸውን የጸጥታ ስጋት ለመቅረፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የሰሜን ወሎ ዞን ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ገለጹ።

36

ወልድያ: የካቲት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የኢትዮጵያን ሰላም እጠብቃለሁ፣ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ” በሚል መሪ መልዕክት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ከዞን ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ከተውጣጡ ሴት የመንግሥት ሥራተኞች ጋር ምክክር አድርጓል።

በምክክሩ ሴቶች በሰላም እጦቱ በሚከሰተው ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በይበልጥ ተጠቂ ስለመኾናቸው ተገልጿል። ሴቶች በሰላም ዙሪያ መምከራቸው አስፈላጊ በመኾኑ መድረኩ ተዘጋጅቷል ያሉት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ኀላፊ ሀያት ዓሊ ናቸው።

ሴት የመንግሥት ሠራተኞች በመንግሥታዊ አገልግሎት የድርሻቸውን በመወጣት ለሰላም መደፍረስ አባባሽ ምክንያቶችን እንዲቀርፉ ግንዛቤን የሚፈጥር መድረክ እንደኾነ ገልጸዋል።
በምክክሩ ሴቶች በዞኑ ሰላምን ለማስፈን የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ሃሳብ መንሸራሸሩንም አንስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ የመንግሥት ሠራተኛ ሴቶች በበኩላቸው ጉዳትን ለመቀነስ ከቤታቸው ጀምረው በመምከር ሰላምን ለማስፈን ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡም አስረድተዋል። እንደ መንግሥት ሠራተኛ መልካም አሥተዳደርን በማስፈን የአካባቢያቸውን የጸጥታ ስጋት ለመቅረፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡም አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል 41 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል የመስኖ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
Next articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 04/2016 ዓ.ም ዕትም