“ክልሉን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለማሸጋገር የተሠራው ሥራ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቷል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ

25

ባሕር ዳር፡ የካቲት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያይቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርዱ በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙን ተከትሎ በቀጣይ በሚከሆኑ ተግባራት ዙሪያ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም፤ ባለፉት ጊዜያት ለዕዙ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አፈፃፀም፣ አዋጁ ከተራዘመ በኋላ ያለው አሁናዊ ክልላዊ ሁኔታ በተለይም ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከመከላከል አኳያ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምክክር ተደርጓል፡፡

ክልሉን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለማሸጋገር የተሠራው ሥራ አንፃራዊ ሰላም ማስገኘቱ እና ሰላሙን ለማፅናት አሁንም ቀሪ ሥራዎች መኖራቸው ተጠቅሷል፡፡

ቦርዱ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ክልሉ በማቅናት ክትትል ማድረጉን በውይይቱ ላይ ማንሳቱን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ በበኩሉ፤ በክልሉ የተመዘገቡና እየተመዘገቡ ያሉ የሠላም ጉዳዮችን፣ ከዚህ በፊት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች የተፈፀሙትንና እየተፈፀሙ ያሉትን ጉዳዮች እንዲሁም መፈፀም ያለባቸው ተግባራትን በዝርዝር አቅርቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።
Next articleየዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርን ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጋር የሚያገናኘው የተከዜ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ተጀመረ።