የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

27

ባሕር ዳር: የካቲት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 15/2016 ዓ.ም የሚቆየውን 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ቀን ውሎው የጥዋት መርሐ ግብሩ የጉባኤው አጀንዳዎች ቀርበው አባላት ከተወያዩ በኋላ እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል።

በመቀጠልም የክልሉ መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወር የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል።

ምክር ቤቱ በሦስት ቀን የጉባኤ ቆይታው የተለያዩ ሪፖርቶችን አድምጦ ያጸድቃል፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፣ የተለያዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት እየተመረቁ ነው።
Next article“ክልሉን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለማሸጋገር የተሠራው ሥራ አንፃራዊ ሰላም አስገኝቷል” የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ