የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተገኙበት እየተመረቁ ነው።

61

ባሕር ዳር፡ የካቲት 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጠራውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሀድሶ ሥልጠና የገቡ የቀድሞ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት እየተመረቁ ይገኛሉ።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ፣ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ፣ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ተገኝተዋል።

ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ለአንድ ሀገር ልማትና እድገት መረጋገጥ አስተማማኝ የሰላም ሁኔታ እና አስተማማኝ የፀጥታ ኀይል የመኖር አስፈላጊነት የሚያጠራጥር አይደለም ብለዋል ።
የፀጥታ ኀይል ለተሰጠው ተልዕኮ እና ኃላፊነት እንዲሁም ሕዝብን ለማገልገል እስከ ሕይዎት መስዕዋትነት መክፈል ይጠበቃልና ለዚህም ዝግጁ መሆን ይገባል ሲሉ በምረቃው ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል። ለሥልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ኮሚሽነር ደስየ ደጀን ምስጋና አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመረዳዳት
Next articleየአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።