የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።

30

ደብረ ማርቆስ: ጥር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በክልሉ የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ተናግረዋል።

“የኢትዮጵያን ሰላም አስጠብቃለሁ ለልጆቼ ምንዳን አወርሳለሁ” በሚል መሪ ሃሳብ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውስጥ የሰላም ውይይት ተካሄዷል።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሴቶች እና ሕጻናት መምሪያ ኀላፊ ወይዘሮ አሞኘሽ መሐመድ በግጭት ወቅት ሴቶች ይበልጥ ተጎጂ ናቸው ብለዋል።

በመኾኑም ሰላምን አጥብቆ መፈለግ እና ለሀገር መረጋጋት አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸዉ ገልጸዋል። ሴቶች ለሰላም በመሥራት ለቀጣዩ ትውልድ ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገርን ማውረስ ይገባልም ብለዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ሴቶች ሰላም የሚጀምረዉ ከራስ እና ከቤተሰብ በመኾኑ የራሳችንን ሰላም መጠበቅ አለብን ነው ያሉት። ከግጭት ትርፍ እንደሌለ በመገንዘብ በአካባቢው እየታየ ያለውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ እንዲኾን እንሠራለን ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የምሥራቅ ጎጃም ዞን እና የጎዛምን ወረዳ የመንግሥት ሠራተኞች የተሳተፉ ሲኾን በዋነኛነት ሴቶች ሰላምን ከማስቀጠል እና ሀገርን ከማረጋጋት አንጻር ስላላቸው ሚና በውይይቱ ተነስቷል።

ዘጋቢ :- ቤተልሄም ተስፋየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከሀሰተኛ መረጃ በመራቅ የአካባቢያቸውን ሰላም እየጠበቁ እንደሚገኙ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ወጣቶች ተናገሩ።
Next articleመረዳዳት