
ከሚሴ: ጥር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገርን እና ሕዝብን ለማደናገር ከሚነዙ ሀሰተኛ መረጃዎች በመራቅ የአካባቢያቸውን ሰላም እየጠበቁ እንደሚገኙ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኙ ወጣቶች ወጣቶች ተናገሩ። ”እኔም ለሀገሬ ዘብ እቆማለሁ” በሚል መሪ ሀሳብ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሚሴ ከተማ የወጣቶች መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተሳተፉ ወጣቶች ለአሚኮ በሰጡት ሀሳብ ወጣቶች በማኅበራዊ ሚድያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እራሳቸውን በማራቅ ለሀገር ዘብ መኾን እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
የሀሰት ትርክት በመፍጠር ወጣቶችን ለጥፋት የሚያነሳሱ አካላት በመኖራቸው ወጣቶች የሚኖሩ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሚፈቱ በማሰብ ከጥፋት ኃይሎች ሴራ ሊርቁ ይገባልም ነው ያሉት።
በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ሊግ ኀላፊ ሁሴን አብዱ ወጣቶች በጥፋት ቡድኖች ሴራ ሳይበገሩ ለአካባቢያቸው ሰላም የሚያደርጉትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ በማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነው ብለዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ሳዳም ሁሴን በበኩላቸው በአፈሙዝ የሚመለስ ጥያቄ ባለመኖሩ በተለይ ወጣቶች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎችን የማቅረብ ባሕልን ሊያዳብሩ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!