
ባሕር ዳር: ጥር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በውይይቱ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፣ የሰሜን ጎጃም ዞን አመራሮች፣ የሰሜን አቸፈር እና የሊበን ከተማ አሥተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።
በሰላም ውይይቱ የተለያዩ የኅብረሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላም እንዲሰፍን ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ለሰላም ዘብ እንቆማለን ብለዋል።
የምሥራቅ ዕዝ 304ኛ ኮር 99ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ወሰን አበበ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ብሔርም ሆነ ሃይማኖት ሳይኖረው ራሱ መስዋእት እየከፈለ ለሀገር እና ለሕዝብ ሰላም እየሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘው ጽንፈኛ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶች ሀገር የማፍረስ ድብቅ አጀንዳ ይዘው ሌት ተቀን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዙ ሕዝብ እያደናገሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሰሜን አቸፈር ወረዳ ሕዝብ ይህን እኩይ ተግባራቸውን በውል ተረድቶ ሰላሙን ሊጠብቅ እንደሚገባም ኮለኔል ወሰን አሳስበዋል።
የሰሜን አቸፈር ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ ስጦታው መርሻ ሰላም የሚጀምረው ከግለሰብ ጀምሮ በመሆኑ ለአካባቢያችን ሰላም መስፈን እያንዳንዳችን የበኩላችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
አቶ ስጦታው ሰላም ወዳዱ የሊበን ከተማ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ነፍጥ አንግበው ከቤታቸው የወጡ ግለሰቦችን በሰላማዊ መንገድ ተመልሰው ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው መደበኛ ሥራቸውን እንዲሠሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።
መረጃው የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!