
ባሕር ዳር: ጥር 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በአባላቱ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች👇
👉 በሀገራችን የሚከሰቱ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግርች አንዱ መንስኤ የኾነውን የተዛባ እና ነጠላ ትርክት ሀገራዊ ትርክት ለመገንባት በሚሠራው ሥራ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥበት? ከሕዝቡስ ምን ይጠበቃል?
👉 መንግሥት የልዩነት ሃሳብ ያላቸውን ኀይሎች የማሰርና የማዋከብ ጫና እያሳደረ ነው ለሚሉ ኀይሎች ምን ምላሽ አለው?
👉 ተጀምረው ያልተጠናቀቁ እና ያልተጀመሩ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ምን የተለየ የመፍትሔ አቅጣጫ ተቀምጧል?
👉 በማዳበሪያ ስርጭት ምዝበራን እና ሕገ ወጥ የማዳበሪያ ንግድን ከመከላከል እና ለአርሶአደሩ ያለ እንግልት በወቅቱ እንዲደርስ ለማድረግ ምን እየተሠራ ነው?
👉 የሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመቆጣጠር መንግሥት ምን እየሠራ ይገኛል?
👉 ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ በተፈራረመችው የወደብ የመግባቢያ ሠነድ የቀጣናው እና አንዳንድ ሀገራት የሚያስተጋቡትን ኢትዮጵያን የሚጎዳ የዲፕሎማሲ ጫና ለማርገብ ምን እየተሠራ ነው?
👉 አንዳንድ የልማት ፕሮጀክቶች ሳይጀመሩ መዘግየት እና ከተጀመሩ በኋላም የመጓተት ሁኔታን ለማረም ምን እየተሠራ ነው?
👉 በአንዳንድ ክልሎች በተከሰተው ድርቅ የዜጎች ህይወት በረሃብ እንዳይቀጠፍ መንግሥት ምን እየሠራ እንደኾነ ቢያብራሩልን።
👉 የስፖርት ጨዋታዎች ውርርድ እየተስፋፋ መምጣቱ ለተለያዩ ችግርች እንደሚዳርግ ይታወቃል። ድርጊቱ የሃገራችን ወጣት የከፋ ችግር ውስጥ ከማስገባቱ በፊት መንግሥት እንዴት ይመለከተዋል?።
👉 የሀገራችን ቱሪዝም ዘርፍ ምዕራባውያን ስለ ሰላማችን በሚያወጡት አፍራሽ መግለጫ ጫና እየተፈጠረበት ይገኛል። ይህንን ታሳቢ በማድረግ የቱሪስት ቁጥር እንዲጨምር እና አዳዲስ መስህቦችን ለማስተዋወቅ ምን እየተሠራ ይገኛል?
👉 ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር ያለውን ፖለቲካዊ ቅራኔን ለመፍታት በመንግሥት በኩል ምን ታስቧል?
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!