
ባሕርዳር: ጥር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ቼልሲ በፕሪሜየር ሊጉ በወልቭስ መሸነፉን ተከትሎ አሠልጣኙ አጣብቂ ውስጥ ገብተዋል።
የለንደኑ ክለብ በሜዳው 4ለ2 መሸነፉን ተከትሎ የክለቡ አመራሮች አርጀንቲናዊውን አሠልጣኝ በሌላ ለመተካት ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ቶክ ስፖርት አስነብቧል።
ቼልሲ በዚህ የውድድር ዓመት በእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ደካማ ጉዞ እያደረገ ነው። በ23 ጨዋታ 31 ነጥቦችን በመሠብሠብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
አሠልጣኝ ማውሪሲዮ ፖቸቲኖ ቼልሲን ከዓመት በፊት ከጀርመናዊው አሠልጣኝ ቶማስ ቱሸል መረከባቸው ይታወሳል።
ቼልሲ አሠልጣኙ ክለቡን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርጉታል በሚል የቀጠራቸው ቢኾንም የታሰበው ግን አልኾነም።
የክለቡ ውጤት ከዛሬ ነገ ይሻሻል ተብሎ ቢጠበቅም በሜዳው ሳይቀር በሰፊ ልዩነት መሸነፉ የክለቡ አመራሮች እና ደጋፊዎች በአሠልጣኙ ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!