
ባሕር ዳር፡ ጥር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር ) ከምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
መረጃውን የላከልን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!