ከወቅታዊ ሁኔታው አንፃር የብዙኃን መገናኛ ኀላፊነት ተሰምቷቸው የሚሠሩበት ጊዜው አሁን እንደኾነ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡

18

ባሕር ዳር፡ ጥር 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የስድስት ወር መደበኛ እና ወቅታዊ ሥራዎች የእቅድ አፈጻጸሙን በኮምቦልቻ ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኀላፊ ህሊና መብራቱ የመድረኩ ዓላማ ባለፉት ስድስት ወራት የተሳኩ ሥራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል እና ድክመት የታየባቸውን ለማስተካከል እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የመገናኛ ብዙኃን ኀላፊነት ተሰምቷቸው የሚሠሩበት ጊዜው አሁን እንደኾነም ነው ያስገነዘቡት፡፡ በመድረኩ የክልሉን የስድስት ወር እቅድ ያቀረቡት የቢሮው የእቅድ ዝግጅት ክትትል እና ግምገማ ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር ፍሬህይወት ተፈራ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አሁናዊ ሁኔታን የተመለከት ሰነድ አቅርበዋል።

ተቋማቸው የቀውስ ጊዜ የዘገባ እስትራቴጅን በመጠቀም ለኅብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃን መስጠት እንደሚጠበቅበት ነው የተናገሩት። ክልሉ በከፊል ስላም ነው ያሉት ዳይሬክተሯ የዲጅታል ሚዲያውን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሕዝብ ግንኙነት ክንፍ ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ አበሻ አንለይ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሴቶች ክልሉ ከገባበት የሰላም እጦት እንዲወጣ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሳሰበ።
Next articleመገናኛ ብዙኀን ለሀገር ጥቅም የሚበጁ እና ኀላፊነት የተሞላባቸው መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ ሀገርን መገንባት እንደሚገባ የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ገለጸ፡፡