ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በናሚቢያው ፕሬዚዳንት ሀጌ ጌንጎብ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ::

9

ባሕርዳር: ጥር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በናሚቢያው ፕሬዚዳንት ሀጌ ጌንጎብ ሕልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለናሚቢያ መንግሥት እና ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል።

የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሀጌ ጌንጎብ በካንሰር መጠቃታቸው ከታወቀ ከሳምንታት በኋላ በ82 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የፌዴራል መንግሥት ከማንም ጋር በሰላም ችግሮችን የመፍታት ፍላጎት አለው” አቶ አሕመድ ሽዴ
Next article“የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው፤ የአማራ ሕዝብ ሰላም ማጣት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም ማጣት ነው” ዶክተር ቢቄላ ሁሬሳ