
“ዛሬ በ15 የአማራ ክልል ከተሞች በተደረጉ ውይይቶች ወደ ክልሉ በመምጣት የሕዝቡን ጥያቄዎች ላዳመጣችሁ የፌደራል እና የሌሎች ክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን እናመሰግናለን። እንዲህ አይነት ውይይቶችን ማካሄድ የአንዱ ችግር ለሌላችንም ችግር መኾኑን እና ለመፍትሔውም በጋራ የምንቆም መኾናችንን ማሳያ ነው። ሕዝብ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለቅሞ በመያዝ በጋራ ለመፍታት እድል የሚሰጥ ነው።
አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር