ስለሰላም ፍቱን ሃሳቦችን ማንሳት፣ መወያየት እና የድርሻን መውሰድ አስፈላጊ እንደኾነ ተገለጸ።

11

ደብረ ብርሃን: ጥር 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በውይይት ለመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እና ክልሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት መግባት እንዲችል ዓላማ ያደረገ ውይይት በደብረ ብርሃን ከተማ ተካሂዷል።

ውይይቱን የመሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር ) ፣ የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፈቃዱ ተሰማ እና በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር) ናቸው።

ውይይቱ ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በውይይት ለመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እና ክልሉ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት መግባት እንዲችል ለማድረግ ያለመ እንደኾነ ተገልጿል።

ከደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና ከሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የውይይቱ ተሳታፊዎች ነበሩ። ተወያዮቹ ከሕዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን በወቅቱ መፍታት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ ሰፊ ውይይቶች መደረግ እንዳለባቸው ያነሱት ተሳታፊዎቹ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም ትኩረት እንዲደረግ ነው የጠየቁት።

በአማራ ክልል የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ማኅበረሰቡን በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት እና ለማኅበራዊ አለመረጋጋትም እንደዳረገው ነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መሥተዳድር እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ አባል ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር ) የተናገሩት።

ስለለሰላም ፍቱን ሃሳቦችን ማንሳት ፣ መወያየት እና የድርሻን መውሰድ አስፈላጊ ነው ያሉት ደግሞ የኦሮምያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፈቃዱ ተሰማ ናቸው።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አሥተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አህመዲን መሐመድ (ዶ.ር) የክልሉን ሰላም ወደ ዘላቂና አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስ በመንግሥት በኩል ለሚወሰዱ የመፍትሄ አማራጮች አጋር መኾን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሰላምን ለማስጠበቅ ማኅበረሰቡ የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ በላይ ተስፋየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከጥላቻና ግድያ የሚያተርፉ የኢትዮጵያ ጠላቶች እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ትርፍ የምናገኘው ከአብሮነትና አንድነታችን መጥበቅ ነው ” የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል
Next articleምስጋና!