“ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የኾነ አስተማማኝ ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ በቀጣይ መሥራት ይጠይቀናል”

8

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ባሕር ዳር፡ ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር በ 6 የሥልጠና ማዕከላት ለፀጥታ መዋቅር አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።

በየደረጃው ለሚገኙ የፀጥታ አመራሮችና አባላት አቅም ለመገንባት፣ ለማጥራትና ለማጠናከር የሚያስችል ሥልጠና መሆኑ ተገልጿል። በሥልጠናው ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው፤ የፀጥታ አካላት በአካባቢያችን በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች በከፈሉት መሥዋእትነት አኹን ያለውን አንፃራዊ ሰላም ማግኘት ተችሏል ብለዋል። ነገር ግን ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የኾነ አስተማማኝ ሰላምን የማረጋገጥ ሥራ በቀጣይ መሥራት ይጠይቀናል ብለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ አያይዘውም የፀጥታ አካላት የተረጋጋ ልማት እንዲመጣ፣ ሕዝቡን ከስጋት፣ ከሁከትና ከሰቀቀን አላቀን ሁሉም ወረዳዎቻችንና ከተሞቻችን በመንግሥት እንዲመሩ ለማድረግ ሰፊ ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰላምና ደኅንነት ዋና መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው ቢሻው፤ የፀጥታ ኀይሉ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ይህ ሥልጠና ወሳኝ መኾኑን አመላክተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለእቴጌ ማስታወሻ፤ ለክብራቸው እጅ መንሻ”
Next article“ፈረስና ፈረሰኛ፣ ጥበብ እና ጥበበኛ በአጅባር”