
አዲስ አበባ: ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና፣ ቀጣናዊ ትስስር ማሳደግ፣ ሰላም እና እድገት ማምጣት በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊላንድ በሚል መሪ መልእክት በድሬዳዋ ወይይት እየተካሔደ ነው።
ቀጣናዊ ትስስር ማሳደግ እና ሰላም እና እድገት ለማምጣት የሚሠራው በምሥራቅ እና ሰሜን ምሥራቅ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ድሬደዋ፣ ጅግጅጋ፣ ቀብሪ ደሀር፣ ሀሮማያ፣ ሰመራ ዩኒቨርስቲዎች፣ ከሶማሌላንድ ሀርጌሳ ዩኒቨርስቲ እና ጅቡቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ነው።
የሰላም ሚኒስትር ድኤታው ኬሬዲን ተዘራ (ዶ.ር) በሀገራት መካከል የሚደረግ ስምምነት ቀጣናውን ለማረጋጋት እና ትብብርን ለማምጣት ይረዳል ብለዋል። በቀጣናው በርካታ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች አሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው መከላከል የሚቻለው መሰል ውይይቶችን ማድረግ ሲቻል ነው ብለዋል
ይህንን ቀጣናዊ ውይይት የከፈቱት የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ሥራዎች ዘላቂ ሰላም ማምጣት ይገባቸዋል የሚለውን የአፍሪካ ኅብረት መርህ መሠረት ተደርጎ ይህ ቀጣናዊ ኮንፈረንስ ስለመዘጋጀቱ ነው ያብራሩት።
ቀጣናው በርካታ የዓለም ሀገራትን የሳበ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል። የቀጣናው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም የቀጣናውን ችግሮች መለየት፣ መመራመር እና ሰላም የሚያመጡ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባቸዋል ነው ያሉት
ኮንፈረንሱ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን፤ የኢትዮጵያ እና የጅቡቲን፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሊላንድን ሰላም እና ትብብርን ያመጣል ብለዋል። ኮንፈረንሱ የሕዝቦች የወደፊት እድገት ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣም አስረድተዋል። በመመካከር ቀጣናውን የተሻለ ድንበሩንም የትብብር ማድረግ ያስፈልጋል ለዚህ ደግሞ ኮንፍንሱ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።
በዚህ ውይይት ላይ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንን ጨምሮ ከጁቡቲ እና ከሶማሊላንድ ምሁራን የተገኙ ሲኾን የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በኮንፈረንሱ እየተሳተፉ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!