ለሀገር ባለውለታ ለኾኑት እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ሐውልት ቆመላቸው።

30

ባሕር ዳር: ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓድዋ ጀግናዋ ንግሥት እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ሐውልት ቆሞላቸዋል። የሐውልት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቄስ መልካሙ ላቀው ስመ ጥር የኾኑ ጀግኖችን መዘከር፣ ለተተኪው ትውልድ ታሪክን ለማስተማር ይረዳል ነው ያሉት። ለእቴጌ ጣይቱ ሐውልት ማቆም ትውልድን ማስተማር፣ ታሪክን ማክበር ነው ብለዋል።

ገድላቸውን መዘከር ስላስፈለገ ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እና በእቴጌ ታሪክ ትውልድን ለማስተማር መኾኑን አንስተዋል።

የካቲት 23/2015 ዓ.ም የመሠረተ ድንጋዩ የተቀመጠለት ሐውልቱ ጥር 25 /2016 ዓ.ም ተመርቋል።

ሐውልቱን በልደታቸው ነሐሴ 12 ቀን ለማስመረቅ ታስቦ እንደነበር እና በጸጥታ ችግር ምክንያት መቆየቱም ተመላክቷል።

ሐውልቱ በከተማዋ ነዋሪዎች እና በመንግሥት በጋራ የተሠራ ነው መኾኑም ተገልጿል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን የእቴጌ ሐውልት የጥንታዊነት እና የታሪካዊነት እውነተኛ ማሳያ መኾኗንም ገልጸዋል። ደብረ ታቦር የመጀመሪያው ኢንዱስትሪ የተሠራባት እና አያሌ ታሪኮች ያሏት ከተማ መኾኗን አመላክተዋል።

የዓድዋ ጀግናዋን ንግሥት ሐውልት ማቆም ታሪክ አክባሪነትን እንደሚያሳይም ገልፀዋል። ሁላችንም ለታሪክና ባሕላችን መጠበቅ ርብርብ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከጸጥታ ኀይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢያቸውን ሰላም እንደሚያስጠብቁ የመሃል ሳይንት ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next article“በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር እና የድንበር ላይ ሰላም ማጠናከር ያስፈልጋል” አቶ ብናልፍ አንዱዓለም