
ደሴ: ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደቡብ ወሎ ዞን ኮማንድፖስት ከመሃል ሳይንት ወረዳ የሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎቸና ከኅብረተሰቡ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ውይይት አካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በጸጥታ ችግሩ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፣ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች ተስተጓጉለዋል። ከግጭት የሚገኝ ትርፍ አለመኖሩን ሁሉም ተገንዝቦ ለሰላም ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባም የውይይቱ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮነን የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችን ሽፋን በማድረግ የተፈጠረው ግጭት ሕዝቡን ለበርካታ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉስቁልና ዳርጎታል ብለዋል።
የአማራ ሕዝብ በሀገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ አስተዋጽኦ ያለውና ጥያቂዎች የሚፈቱበትን መንገድ የሚያውቅ መኾኑንም ገልጸዋል።
ችግሮች በሰላማዊ ምንገድና በንግግር መፍትሔ እንዲያገኙም ኅብረተሰቡ ከምቸውም ጊዜ በላይ መሥራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል። ለሰላም ቅድሚያ በመስጠትም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:–ደጀን አምባቸው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!