እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ ሐውልት ቆመላቸው።

47

ደብረ ታቦር፡ ጥር 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል።

እቴጌ ጣይቱ የተወለዱት ነሐሴ 12/1832 ዓ.ም በበጌምድር ደብረ ታቦር ነው። እቴጌዋ በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነስተዋል። በዚሁ ታላቅ እና ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ዳዊት ተምረዋል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ስም ያላቸው እቴጌ ጣይቱ በዓድዋ ድል ከፍ ያለ ተግባር ፈጽመዋል። በፖለቲካ፣ በወታደራዊ እና በሌሎች ተግባሮች አያሌ ታሪኮችን ሠርተዋል።

እቴጌዋ ለሠሩት መልካም ተግባር በትውልድ ከተማቸው ሐውልት ቆሞላቸዋል። ሐውልቱ በከተማዋ ነዋሪዎች እና በመንግሥት ወጪ መሠራቱም ተመላክቷል። ለሐውልቱ 13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን ለአሚኮ ገለልጸወል።

የእቴጌዋ ሐውልት በትውልድ ከተማቸው መቆም ትውልዱ ታሪክን እንዲያውቅ፣ ለሀገር ፍቅር የተከፈለውን መስዋዕት እንዲረዳ ያደርገዋል ተብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበመካከር እና በመግባባት የቀደመ ሰላማችንን እንመልሳዋለን ሲሉ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
Next articleከጸጥታ ኀይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢያቸውን ሰላም እንደሚያስጠብቁ የመሃል ሳይንት ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።