
ባሕርዳር: ጥር 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ተጋጣሚዎችን የሚለዩ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ።ምሽት 2ሰዓት በሚጀምር ጨዋታ ናይጀሪያ ከአንጎላ ይጫወታሉ።የናይጀሪያ ብሔራው ቡድን በጥሎ ማለፍ ጨዋታ ካሜሮንን በማሸነፍ ነው ለሩብ ፍጻሜ የበቃው።
የአንጎላ ብሔራዊ ቡድን አልጀሪያ፣ቦርኪናፋሶና ሞሪታኒያን በያዘው ጠንካራ ምድብ የምድቡ አሸናፊ በመኾን ጥንካሬውን አሳይቷል።በጥሎ ማለፉም ናምቢያን 3ለ0 በኾነ ውጤት ረቷል።
በሌላ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከጊኒ ይገናኛሉ።ኮንጎ ጠንካራዋ ጎብጽን በመለያ ምት በመርታት ነው ከዚህ የደረሰችው።
ጊኒ ደግሞ ኢኳቶሪያል ጊኒን 1ለ0 በመርታት ስምንቱን መቀላቀሏ ይታወሳል።የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 5ሰዓት ይጀምራል።
በአስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!