የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ለስድስት ወራት የታወጀው አስቸኳይ አዋጅ ለአራት ወራት ተራዘመ።

24

ባሕር ዳር፡ ጥር 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት አራዝሞታል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በርካታ ለውጦችን ማምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተጨማሪ ስራዎች በመኖራቸው ምክንያት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማራዘም አስፈልጓል ተብሏል።

የምክር ቤቱ አባላት ውይይት ካደረጉበት በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ ከዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ለአራት ወራት ተራዝሟል።

በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት የስራ ጊዜ ለማራዘም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ፀድቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአካባቢያቸውን ጸጥታ የማረጋገጥ ኀላፊነታቸውን እንደሚወጡ የደጀን ዙሪያ እና የደጀን ከተማ አሥተዳደር ሠልጣኝ የጸጥታ አካላት ገለጹ።
Next article“አጅባር:- ምስጢር የተገለጠበት፤ ንጉሥ የሠረገበት”