
እንጅባራ: ጥር 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ በዓል ”የሰላም አርበኝነት ለወንድማማችነት” በሚል መሪ ሃሳብ ለ84ኛ ጊዜ በእንጅባራ ተከብሯል። በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁንም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ገልጿል።
የመምሪያው ኀላፊ ጌታቸው ቢሻው 84ኛው የአገው ፈረሰኞች ዓመታዊ በዓል ታሪካዊ እና ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም መከበሩን ተናግረዋል። በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተሳትፎ ለነበራቸው የጸጥታ ተቋማት፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ለሰላም ወዳዱ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሕዝብ ምሥጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!