
አዲስ አበባ: ጥር 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት እና የፕላንና ልማት ኮሚሽን አዲስ የስታስቲክስ ልማት ፕሮግራም አስጀምረዋል። ይህ ፕሮግራም የሀገሪቱን የ10 ዓመት ዕቅድ እና ለሁለተኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ያግዛል ተብሏል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) ፕሮግራሙ ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም የሚተገበር መኾኑን አስታውቀዋል። ፕሮግራሙ እስካሁን ከሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ያልዘለለውን የመረጃ አያያዝ ወደ ግብርና ተግባራትም ያሸጋግራል፤ በቴክኖሎጂም ይደግፋል ነው ያሉት።
ይህን ብሔራዊ የስታስቲክስ ሥርዓት ወደ ዘመናዊ ግልጽነት እና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚመራ እንዲኾንም የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተውለታል ተብሏል። አሠራሩ የሕግ እና ተቋማዊ ማዕቀፎችን ማጠናከር እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መተግበርን አካትቶ ይቀጥላል ተብሏል።
በስታስቲክስ ዘርፉ ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ጽናት እና ብልጽግና ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትሯ ሀገራዊ የልማት ተግባራቶቻችን በመረጃ የተደገፉ እንዲኾኑ ወሳኝነት አለው ብለዋል።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!