የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራውን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አስጀመረ።

36

ደብረ ብርሃን: ጥር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የዘንድሮውን የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አካሄዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሠብሣቢ ብርጋዴር ጄኔራል አበባው ሰይድን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ እና የተፋሰስ ልማት ሥራ በዞኑ በየዓመቱ በስፋት እየተሠራ ይገኛል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ የሚሠራውን የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ጥራቱን በማረጋገጥ እና ሽፋኑን በማሳደግ የአርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከ660 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለማፍላት በሂደት ላይ መኾኑም ገልጸዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ታደሰ ማሙሽ የዘንድሮውን የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲሠሩ መቆየቱን ተናግረዋል።

በዞኑ ከ1 ሺህ በላይ በሚኾኑ ተፋሰሶች የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራውን ለመሥራት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ማካሄዳቸውን ነው የተናገሩት።

በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላና ጠራ ወረዳ የሩክሲ ጮንጮ ቀበሌ አርሶ አደሮች ይህንን ተግባር ለዓመታት በስፋት ሲሠሩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የተሠራው ሥራ የአፈር ለምነትን በመጠበቅ ምርት እና ምርታማነታቸው እንዲያድግ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአካባቢውን ሰላም የሚያረጋገጥ ብቁ የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት እየሠራ መኾኑን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“የመርቆሬዎስን በዓል በደመቀ ኹኔታ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቀናል” የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር