የአካባቢውን ሰላም የሚያረጋገጥ ብቁ የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት እየሠራ መኾኑን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።

33

ከሚሴ: ጥር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለጸጥታ መዋቅሮች ሥልጠና መሰጠት ተጀምሯል። በደዋጨፋ ወረዳ ወለዲ ከተማ የሥልጠናው መክፈቻ ተካሂዷል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብደላ አሕመድ የብሔረሰብ አሥተዳደሩን ሰላም ለማረጋገጥ ብቁ የኾነ የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት እየሠራ ነው ብለዋል።

የሕዝብን እና የሀገርን ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል። ለጸጥታ መሪዎች እና አባላት የሚሰጠው ሥልጠና በአምስት ማዕከላት ለ10 ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።

በመክፈቻው ላይ የተገኙት የደዋጨፋ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አብዱ መሐመድአሚን ለነገ የተሻለ ሀገር ለመፍጠር ወሳኝነት ያለው ጠንካራ የጸጥታ መዋቅር ለመገንባት እየተሠራ ነው ብለዋል። የወረዳው ሕዝብ ከመንግሥት ጋር በመኾን ለሰላም እየሠራ ስለመኾኑም ተናግረዋል።

በመከላከያ ሠራዊት የ102ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ኦፕሬሽናል አዛዥ ኮሎኔል ሰለሞን ፀጋዬ ሥልጠና እየወሰዱ ያሉ የጸጥታ አባላት ሕዝብን ከሕዝብ የሚነጣጥሉ የጥፋት ኃይሎችን ለማረም አቅም እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተገኘውን ሰላም ማጽናት እና ማስቀጠል እንደሚገባ የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ተናገሩ።
Next articleየሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራውን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ አስጀመረ።