
ወልድያ: ጥር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለወልድያ ከተማ አሥተዳደር የጸጥታ ግብረ ኃይል ለ10 ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።
ሥልጠናው የከተማ ፖሊስ፣ አድማ ብተና ፖሊስ እና የክፍለ ከተማው አጠቃላይ የጸጥታ መዋቅር የሚሳተፉበት መኾኑን የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ዘመዴነህ ግርማው ገልጸዋል፡፡
ኀላፊው በሥልጠናው ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና ከተማ አቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች እንደሚዳሰሱም አስገንዝበዋል።
የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ ረገድ ሕዝቡም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የሥልጠና ተሳታፊዎች የነበረውን የአመለካከት ብዥታ፣ የመረጃ ክፍተትን እና የግንዛቤ ውስንነትን ሥልጠናው ይቀርፋል ሲሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- ካሳሁን ኃይለሚካኤል
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!