
ደሴ: ጥር 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ መርሐ ግብሩን በገራዶ 016 እንዶድ በር ቀበሌ በይፋ አስጀምሯል።
በተፋሰስ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ምርታማነትን ለማሳደግ ከተማ አሥተዳደሩ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ እዮኤል ሙሉዬ የተፈጥሮ ሃብት ሥራው በ10 ቀበሌዎች በሚገኙ 12 ተፋሰሶች ላይ እንደሚሠራ ተናግረዋል። ይህ የተፈጥሮ ሃብት ሥራ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡
የልማቱ ተሳታፊ የኾኑት የ016 ቀበሌ አርሶ አደሮች ከዚህ በፊትም የተፈጥሮ ሃብት ሥራን ሲያከናውኑ እንደነበር ገልጸው በቀጣይም የአፈር ለምነትን ለመጠበቅ ዝግጁ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- መሐመድ በቀለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!