
ባሕር ዳር: ጥር 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆኦርጂያ ሜሎኔ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀቀናዊ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ውይይት በማድረጋችን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆኦርጂያ ሜሎኔን አመሰግናቸዋለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተጠናክረው የቀጠሉት ግንኙነቶቻችን በሁለቱ ሀገሮች መካከል እያደገ ለመጣው ትብብር ዋቢ ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!