በሀገር ውስጥ የክትባት መድኃኒት ማምረት የሚያስችል ፍብሪካ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

23

አዲስ አበባ: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመኾን በሀገር ውስጥ የተለያዩ የክትባት መድኃኒቶችን ማምረት የሚያስችል ፍብሪካ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጧል።

የመጀመሪያ የኾነው የተለያዩ የክትባት መድኃኒቶች ማምረቻን ለመገንባት “የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ” ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ በቂልንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተቀምጧል።

በኮሮና ወረርሽኝ ጊዜ የነበረው የክትባት መድኃኒቶች እጥረት ትምህርት የሰጠ በመኾኑ በሀገር ውስጥ መድኃኒቶችን ለማምረት እቅድ ተይዞ ወደ ሥራ ለመግባት መወሰኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ ሲገባ በሀገር ውስጥ ያለውን የክትባት መድኃኒቶችን እጥረት ለመቅረፍ እና የሀገሪቱን የጤና ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያስችልም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ መመረት ሲጀምሩ ከራስ አልፎ በአህጉሩ ያለውን የመድኃኒት እጥረት ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መኾኑንም ነው ያስገነዘቡት።
ፕሮጀክቱን ለማሳካት ትልቅ ትብብር እያደረጉ ለሚገኙ አጋሮችም ያላቸውን ምሥጋና አቅርበዋል።

በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የዓለም የጤና ድርጅት፣ የዓለም ባንክ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ እየተሳተፉ ነው።
Next article“የተባበረ የሕዝብ እና የመንግሥት አቅም ለዘላቂ ልማት መረጋገጥ ዋስትና ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን