ዚነዲን ዚዳን የአልጄሪያን ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እንዲያሠለጥን ተጠየቀ፡፡

29

ባሕር ዳር: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ድንቅ ተጫዋች ፈረንሳዊው ዚነዲን ዚዳን በቅርቡ ከአልጀሪያ ብሔራዊ ቡድን ኀላፊነታቸው በለቀቁት ጃሜል ቤልማዲ ምትክ ቡድኑን እንዲያሠለጥን ከአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥያቄ ቀርቦለታል፡፡

ቤልማዲንን ለመተካትም ከዚነዲን ዚዳን በተጨማሪ ለሄርቬ ሬናርድ እና ቫሂድ ሃሊልሆዲችም ጥያቄ እንደቀረበላቸው ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

የአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዋሊድ ሳዲ “በርካታ ባለሙያዎችን ብናጭም ዚነዲን ዚዳን ግን የአልጄሪያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለማሠልጠን የሚያስችሉ መስፈርቶቻችንን የሚያሟላ በመኾኑ ይመጥናል” ሲሉ መደመጣቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

ዚዳንም በወላጆቹ ሀገር ለቀረበለት ጥያቄ አመሥግኖ “የአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድንን ለማሠልጠን ለእኔ ጊዜ አሁን አይደለም” ብሏል፡፡

እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር 2023 ዚነዲን ዚዳን የዩናይትድ ስቴትስን ብሔራዊ ቡድን ለማሠልጠን የቀረበላቸውን ጥያቄም ውድቅ ማድረጋቸውንም ዴይሊ ሜይል አስታውሷል፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቆዬው ባሕል እና እሴት በመመካከር ችግሮችን መፍታት ይገባናል” ወይዘሮ ገነት ወንድሙ
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በጣልያን-አፍሪካ ጉባኤ እየተሳተፉ ነው።