በሐይቅ ከተማ አሥተዳደር የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

31

ደሴ: ጥር 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በክልል፣ በከተሞች ተቋማዊ እና መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም (ዩ አይ አይ ዲ ፒ) እና በከተማ አሥተዳደሩ በጀት ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች በሐይቅ ከተማ ተመርቀዋል።

የቢሮ ሕንጻ እና የነዳጅ ማደያ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የከተማ አሥተዳደሩን አገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጠ ለማድረግ ታስቦ የተገነባው የቢሮ ሕንጻ 56 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ነው።

የተገልጋዮችን እንግልት ለማስቀረት እንደሚያግዝም ተገልጿል። ግንባታው በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ መጠናቀቁንም የሐይቅ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከድር መሐመድ ተናግረዋል።

በከተማ አሥተዳደሩ በ21 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የነዳጅ ማደያም ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።የነዳጅ ማደያው መገንባት የከተማዋን እድገት ለማፋጠን ያስችላልም ተብሏል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ አሊ ይመር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሙሉ አቅማችን ለጋራ ዓላማችን ስኬት እንሥራ” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next article“በቆዬው ባሕል እና እሴት በመመካከር ችግሮችን መፍታት ይገባናል” ወይዘሮ ገነት ወንድሙ